ደብል ቻንስ ወይም ድርብ ዕድል ምንድነው? እንዴት መጫወት ይቻላል?

እንደሚታወቀው በአንድ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉት የውጤት አይነቶች ሦስት ናቸው። እነሱም፦ 

  1. ባለሜዳው ቡድን ያሸንፋል (1)
  2. አቻ ይወጣሉ (x)
  3. ከሜዳው ውጭ የሚጫወተው ቡድን ያሸንፋል (2)

ከእነዚህ ውጤቶች መካከል ሁለቱን ዕድሎች በአንድ ጊዜ ለመምረጥ የሚያስችለው ምርጫ ደብል ቻንስ ወይም ድርብ ዕድል ይባላል። ይህ ምርጫ ሁለት ዕድሎችን አቅፎ ስለሚይዝ በብዙ ተወራራጆች ዘንድ ከፍተኛ ተፈላጊነት አለው።

ደብል ቻንስ ወይም ድርብ ዕድል ሦስት አማራጮች አሉት፡፡ እነሱም፦

  1. ባለሜዳው ቡድን ያሸንፋል ወይም አቻ ይወጣሉ። ይህም ምርጫ በምልክት ሲቀመጥ 1X (1ወይምX) ይባላል።

በዚህ ምርጫ መሠረት ከሜዳው ውጭ የሚጫወተው ቡድን ካሸነፈ ብቻ ምርጫው አይሳካም።

  • ከሜዳው ውጭ የሚጫወተው ቡድን ያሸንፋል ወይም አቻ ይወጣሉ። ይህም ምርጫ በምልክት ሲቀመጥ 2X (2ወይምX) ይባላል።

በዚህ ምርጫ ላይ ባለሜዳው ቡድን ሲያሸንፍ ብቻ ምርጫው አይሳካም።

  • ባለሜዳው ቡድን ወይም ከሜዳው ውጭ የሚጫወተው ቡድን ያሸንፋል። ይሕም ምርጫ በምልክት ሲቀመጥ 12 (1ወይም2) ይባላል።

በዚህ ምርጫ ላይ ጨዋታው በአቻ ውጤት ካለቀ ብቻ ምርጫው አይሳካም።

BestBet Accumulator Bonus WIN UP TO 100%

X