Champions League Tips

[lPrediction in=”Champions League”]

የቻምፒየንስ ሊግ የ2021/22 የውድድር ዘመን ምልከታ

በእግር ኳሱ ዓለም ከሚደረጉ ውድድሮች መካከል በትልቅ ጉጉት የሚታየው እና የሚጠበቀው የቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ሃያላን የአውሮፓ ክለቦችን አሰልፎ በታላቅ ድምቀት መካሄዱን ቀጥሏል፡፡ የብዙ ክለቦች ህልም የሆነውን ዋንጫ ለማንሳት በሚደረገው ፍልሚያ 32 ክለቦች ይሳተፉበታል፡፡

አሁን ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ በሚደረጉ የጥሎ ማለፍ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ላይ የምንገኝ ሲሆን ከወዲህ ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ አንዳንድ ክለቦችም ተለይተዋል፡፡ የስድስት ጊዜ ባላንዶር አሸናፊውን ሊዮኔል ሜሲን ጨምሮ ኔይማር እና ምባፔን ያጣመረው ፒኤስጂ ለዋንጫ ሲጠበቅ በሪያል ማድሪድ ከውድድሩ ተባሯል፡፡ የ13 ጊዜው ሻምፒዮን ማድሪድ የሚያስፈራ ስብስብ ባይይዝም ልምዱን ተጠቅሞ የሩብ ፍጻሜ ቦታውን አመቻችቷል፡፡ የእንግሊዞቹ ማን ሲቲ እና ሊቨርፑልም ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፋቸውን ካረጋገጡት ክለቦች ውስጥ የተካተቱ ሲሆን ባየርን ሙኒክም ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል፡፡

ያምናው ሻምፒዮን ቼልሲ ከሊል የሚያደርገውን ግጥሚያ ጨምሮ ሌሎች ቀሪ የሩብ ፍጻሜ ቦታዎችን ለማግኘት የሚደረገው ፍልሚያ ማን ዩናይትድን ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ የጣሊያኑ ሃያል ጁቬንቱስን ከቪላሪያል እንዲሁም አያክስን ከቤንፊካ አፋጧል፡፡ የውድድሩን አሸናፊ ለመገመት ጊዜው ገና ቢሆንም ምርጥ አቋም ላይ የሚገኘው የፔፕ ስብስብ፣ እያደር እየጠነከረ የመጣው የሳላህ ሊቨርፑል እንዲሁም ፒኤስጂን ያንበረከከው ማድሪድ ዋንጫው ላይ እጃቸውን የማሳረፍ የተሻለ ዕድል እንዳላቸው ይታመናል፡፡ 

Win 100K ETB Everyday from Betika

X