Preview Match Day 16

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅድመ ዳሰሳ

Friday April 1

ዓርብ መጋቢት 23

መከላከያ ከአርባምንጭ ከነማ

በመጀመሪያው ዙር 15 ጨዋታዎች እኩል 18 ነጥብ መሰብሰብ የቻሉት ሁለቱ ተጋጣሚዎች በሊጉ ሰንጠረዥ ላይ በሦስት ጎል ልዩነት ተበላልጠው 10ኛ እና 11ኛ ደረጃን ተከታትለው ይዘዋል፡፡ ካደረጓቸው ጨዋታዎች ዘጠኙን በአቻ የተለያዩት አርባምንጭ ከነማ በሊጉ ዝቅተኛ ጎል ካስተናገዱ ክለቦች ውስጥ ስማቸው ይጠራል፡፡ ምንም ጥሩ የመከላከል ብቃት ቢያሳዩም በማጥቃቱ ረገድ የነበራቸው ደካማ እንቅስቃሴ ውጤታቸውን ቀንሶታል፡፡ በመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ ከ12ኛ ደረጃ ወደ 11ኛ ማደግ የቻለው መከላከያ በበኩሉ ከፍ ዝቅ በሚል የጨዋታ እንቅስቃሴ የውድድሩን የመጀመሪያ ዙር አጠናቋል፡፡

ግምት

ጨዋታው ያለግብ አቻ የመጠናቀቅ እድል አለው፡፡

Friday April 1

ዓርብ መጋቢት 23

ወልቂጤ ከተማ ከ አዳማ ከተማ

በሊጉ ሰንጠረዥ ወገብ ላይ የሚገኘውና በመጀመሪያ ዙር ውድድር መካከለኛ ደረጃ አቋም ሲያሳይ የነበረው አዳማ ከተማ ካጋጠመው ሁለት ሽንፈት በስተቀር አብዛኛውን ጨዋታውን በአቻ ውጤት ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ ወልቂጤ ከተማ ካደረጋቸው 15 ጨዋታዎች መካካል አምስቱን አሸንፎ፣ በአምስቱ ተሸንፎ፣ አምስቱን አቻ ወጥቷል፡፡ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት አንድ ብቻ ሲሆን አዳማ በ21 ነጥብ 6ኛ፤ ወልቂጤ ደግሞ በ20 ነጥብ 9ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ የክለቦቹን የእርስ በእርስ የመጨረሻ 5 ጨዋታ ስንመለከት አዳማዎች ሁለቴ ሲያሸነፉ፣ ወልቂጤ አንድ ጊዜ አሸንፏል፤ ቀሪውን ሁለት ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቀዋል፡፡

ግምት

አዳማ ከተማ በደጋፊው ፊት መጫወቱ የተሻለ ዕድል ቢፈጥርለትም ቡድኖቹ ካላቸው ተቀራራቢ አቋም በመነሳት ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ይጠናቀቃል የሚል ግምት አለ፡፡

Saturday April 2

ቅዳሜ መጋቢት 24

ወላይታ ድቻ ከድሬዳዋ ከተማ

በዋንጫ ፉክክር ውስጥ በጉልህ እየተሳተፈ የሚገኘው ወላይታ ድቻ በመጀመሪያ ዙር ያደረገውን ድንቅ እንቅስቃሴ ማስቀጠል ከቻለ ዋንጫውን የማንሳት ዕድል ይኖረዋል፡፡ በጠባብ የጎል ልዩነት እያሸነፉ ሶስት ነጥብ ከጨዋታዎች የሰበሰቡት ድቻዎች ካደረጓቸው የመጨረሻ አምስት ጨዋታዎች አራቱን ሲያሸንፉ በአንዱ ብቻ ተሸንፈዋል፡፡ የመጀመሪያውን ዙር 6 ሳምንት ጨዋታዎች ያስተናገዱት ድሬዳዎች በበኩላቸው በደጋፊዎቻቸው ፊት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ አቅቷቸዋል፡፡ ካደረጉት ስድስት ጨዋታ አንዱን ብቻ ሲያሸንፉ ሁለት ጊዜ ተሸንፈው የተቀረውን አቻ ወጥተዋል፡፡

ግምት

ወላይታ ዲቻ በጠባብ የጎል ልዩነት ጨዋታውን ያሸንፋል፡፡

Saturday April 2

ቅዳሜ መጋቢት 24

ጅማ አባ ጅፋር ከሃዋሳ ከተማ

በሊጉ የመጨረሻ ጨዋታዎች ጥሩ የአቋም ለውጥ እያሳዩ የነበሩት ጅማዎች ከገቡበት የመውረድ አደጋ ለመውጣት አሁንም ራሳቸውን ማሻሻልና ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በሊጉ ያገኟቸውን ሶስት ብቻ ድሎች ማስመዝገብ የቻሉት በመጨረሻዎቹ ስድስት ጨዋታዎች ሲሆን ደረጃቸውንም ሰበታ ከተማን በመብለጥ ከ16ኛ ደረጃ ወደ 15ኛ ደረጃ አሳድገዋል፡፡ ሀዋሳ ከተማ በዋንጫ ፉክክር ቀጥተኛ ተሳትፎ ከሚያደርጉ ክለቦች አንዱ ነው፡፡ ቡድኑ በዘንድሮው ውድድር ከዋንጫ ባሻገር ለካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ለማለፍ ከወላይታ ድቻ ጋር ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

ግምት

ሀዋሳ ከተማ የተሻለ የማሸነፍ ግምት ቢሰጠውም ጅማ አባ ጅፋር ያልተጠበቀ ድል ሊያስመዘግብ ይችላል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ከእረፍት የተመለሰው የኢትዮጵያ ሊግ ውድድር 17ኛ ሳምንት መርሃ-ግብር በዚህ ሳምንት ቀጥሎ ይካሄዳል፡፡ በ16ኛ ሳምንት ዙር ከተካሄዱ ስምንት ጨዋታዎች መካከል አምስቱ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል፡፡ ሊጉን የሚመሩት ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ወላይታ ዲቻ እና ሃዋሳ ከተማ ብቻ ድል ቀንቷቸዋል፡፡ የሊጉ የ17ኛ ሳምንት ዙር ጨዋታዎች ከቀን ማክሰኞ መጋቢት 27 ጀምሮ እስከ ዓርብ መጋቢት  30 ድረስ ይካሄዳሉ፡፡ የጨዋታዎቹን ቅድመ ዳሰሳና ግምት ከዚህ በታች ተመልክተናል፡፡

ማክሰኞ መጋቢት 27 ቀን 2014

ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ

Ethiopian Coffee vs St. George

ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለቦች መካከል በደጋፊ ብዛት አቻ የሌላቸው የሁለቱ ቡድኖች የሸገር ደርቢ ጨዋታ ማክሰኞ ይደረጋል፡፡ ምንም እንኳን ጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለዋንጫ እየገሰገሰ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ወጥ አቋም ማሳየት በተቸገረበት ወቅት ቢደረግም በክለቦቹ መካከል ያለው የባላንጣነት ታሪክ ጨዋታውን ተጠባቂ ያደርገዋል፡፡ ቡናዎች ያለፉትን ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም፡፡ ጊዮርጊስ በአንጻሩ ካለፉት አምስት ጨዋታዎች ውስጥ ሶስቱን አሸንፎ በሁለቱ አቻ ወጥቷል፡፡ በቅርብ ጊዜ በተደረጉ አምስት የእርስ በርስ ግጥሚያዎች ጊዮርጊሶች የመጨረሻውን ጨዋታ ጨምሮ ሶስት ጊዜ ሲያሸንፉ ቡናዎች ማሸነፍ የቻሉት አንድ ጊዜ ብቻ ነው፤ የቀረውን አንድ ጨዋታ በአቻ ተጠናቋል፡፡

ግምት

ከሁለቱ ተጋጣሚዎች የጨዋታ ታሪክ እና የቅርብ ጊዜ አቋም በመነሳት ጊዮርጊስ ጨዋታውን የማሸነፍ ሰፊ እድል አለው፡፡

ማክሰኞ መጋቢት 27 ቀን 2014

መከላከያ ከሰበታ ከተማ

Defence FC vs Sebeta City

ከሊጉ የመውረድ አደጋው ከጨዋታ ጨዋታ እየሰፋ የመጣው ሰበታ ከተማ ባለፈው ሳምንት ጨዋታም ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ ቡድኑ በዚሁ ደካማ እንቅስቃሴው ከቀጠለ ከፕሪምየር ሊጉ መውረዱ አይቀሬ ይመስላል፡፡ ከ16 ሳምንት ዙር ጨዋታዎች በኋላ 9 ነጥቦችን ብቻ ይዞ ከ16 የግብ እዳ ጋር የሊጉ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ መከላከያዎች ምንም እንኳን ከአደጋው ዞን ውጭ ቢሆኑም ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው ለማለት  ያስቸግራል፡፡ ከመጨረሻ አምስት ጨዋታዎችም ማሸነፍ የቻሉት አንዱን ብቻ ነው፡፡ ጦሮቹ በ19 ነጥብ እና ሶስት የግብ እዳ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ግጥሚያ መከላከያ 1-0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ግምት

ሁለቱም ቡድኖች ጥሩ አቋም ላይ ባይሆኑም መከላከያዎች በንጽጽር የተሻሉ በመሆናቸው ጨዋታውን በጠባብ ውጤት ያሸንፋሉ፡፡

ረቡዕ መጋቢት 28 ቀን 2014

ፋሲል ከነማ ከወልቂጤ ከተማ

Fasil Kenema vs Welkite City

የአምናው ሻምፒዮን ፋሲል ከነማ ቀስ በቀስ ከዋንጫው ፉክክር እየራቀ ይመስላል፡፡ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለው የነጥብ ልዩነትም ሰባት ደርሷል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ባደረገው ጨዋታ ወሳኝ ነጥብ ጥሎ ወጥቷል፡፡ በቅርብ ጊዜ ካደረጋቸው አምስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ፋሲሎች የዋንጫ ተስፋቸውን ለማስቀጠል ከወዲሁ ወደ ድል መንገድ መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ወልቂጤ አሁንም በሊጉ ሰንጠረዥ ወገብ ላይ ተደላድሎ ተቀምጧል፡፡ በ21 ነጥብ 9ኛ ደረጃን ይዟል፡፡ ከአዳማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል፡፡ በቅርብ ጊዜ ግንኙነታቸው ፋሲል ከነማ 1-0 አሸንፏል፡፡

ግምት

ፋሲል ከነማ ከተጋጣሚያቸው ከባድ ፈተና ቢገጥማቸውም ጨዋታውን በጠባብ የጎል ልዩነት ጨዋታውን ያሸንፋሉ፡፡

ረቡዕ መጋቢት 28 ቀን 2014

ባህር ዳር ከተማ ከሀዲያ ሆሳዕና

Bahir Dar City vs Hadiya Hosaena

ተከታታይ አራተኛ ጨዋታቸውን በአቻ የተለያዩት ባህር ዳሮች አሁንም በሚጠበቅባቸው የውጤት መንገድ መሄድ አልቻሉም፡፡ በሊጉ የአደጋ ዞን የሚገኘውን አዲስ አበባ ከተማ የገጠመው ቡድኑ ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ይዞ ለመውጣት በድጋሚ ተቸግሯል፡፡ ቡድኑ የመጨረሻ ድሉን ያገኘው ከአራት ጨዋታ በፊት ነበር፡፡ ሀዲያ ሆሳዕናዎች  ከተከታታይ ሽንፈት መልስ ከፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋርተው መውጣት ችለዋል፡፡ መሪው ጊዮርጊስንም ከሶስት ጨዋታ በፊት ነጥብ ማስጣላቸው ይታወሳል፡፡ 18 ነጥብ ይዘው በሊጉ ሰንጠረዥ ላይ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሆሳዕናዎች በጥሩ አቋም ስማቸው ባይነሳም ከትልቅ ተጋጣሚዎች ጋር በተደጋጋሚ ነጥብ መውሰድ ችለዋል፡፡ በቡድኖቹ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ 1-0 በሆነ ውጤት አሸንፎ ነበር፡፤

ግምት

ባህር ዳር ከተማ በድጋሚ ከተጋጣሚያቸው ጋር አቻ ይለያያሉ፡፡

BestBet Accumulator Bonus WIN UP TO 100%

X