Preview Match Day 16

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅድመ ዳሰሳ

Friday April 1

ዓርብ መጋቢት 23

መከላከያ ከአርባምንጭ ከነማ

በመጀመሪያው ዙር 15 ጨዋታዎች እኩል 18 ነጥብ መሰብሰብ የቻሉት ሁለቱ ተጋጣሚዎች በሊጉ ሰንጠረዥ ላይ በሦስት ጎል ልዩነት ተበላልጠው 10ኛ እና 11ኛ ደረጃን ተከታትለው ይዘዋል፡፡ ካደረጓቸው ጨዋታዎች ዘጠኙን በአቻ የተለያዩት አርባምንጭ ከነማ በሊጉ ዝቅተኛ ጎል ካስተናገዱ ክለቦች ውስጥ ስማቸው ይጠራል፡፡ ምንም ጥሩ የመከላከል ብቃት ቢያሳዩም በማጥቃቱ ረገድ የነበራቸው ደካማ እንቅስቃሴ ውጤታቸውን ቀንሶታል፡፡ በመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ ከ12ኛ ደረጃ ወደ 11ኛ ማደግ የቻለው መከላከያ በበኩሉ ከፍ ዝቅ በሚል የጨዋታ እንቅስቃሴ የውድድሩን የመጀመሪያ ዙር አጠናቋል፡፡

ግምት

ጨዋታው ያለግብ አቻ የመጠናቀቅ እድል አለው፡፡

Friday April 1

ዓርብ መጋቢት 23

ወልቂጤ ከተማ ከ አዳማ ከተማ

በሊጉ ሰንጠረዥ ወገብ ላይ የሚገኘውና በመጀመሪያ ዙር ውድድር መካከለኛ ደረጃ አቋም ሲያሳይ የነበረው አዳማ ከተማ ካጋጠመው ሁለት ሽንፈት በስተቀር አብዛኛውን ጨዋታውን በአቻ ውጤት ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ ወልቂጤ ከተማ ካደረጋቸው 15 ጨዋታዎች መካካል አምስቱን አሸንፎ፣ በአምስቱ ተሸንፎ፣ አምስቱን አቻ ወጥቷል፡፡ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት አንድ ብቻ ሲሆን አዳማ በ21 ነጥብ 6ኛ፤ ወልቂጤ ደግሞ በ20 ነጥብ 9ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ የክለቦቹን የእርስ በእርስ የመጨረሻ 5 ጨዋታ ስንመለከት አዳማዎች ሁለቴ ሲያሸነፉ፣ ወልቂጤ አንድ ጊዜ አሸንፏል፤ ቀሪውን ሁለት ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቀዋል፡፡

ግምት

አዳማ ከተማ በደጋፊው ፊት መጫወቱ የተሻለ ዕድል ቢፈጥርለትም ቡድኖቹ ካላቸው ተቀራራቢ አቋም በመነሳት ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ይጠናቀቃል የሚል ግምት አለ፡፡

Saturday April 2

ቅዳሜ መጋቢት 24

ወላይታ ድቻ ከድሬዳዋ ከተማ

በዋንጫ ፉክክር ውስጥ በጉልህ እየተሳተፈ የሚገኘው ወላይታ ድቻ በመጀመሪያ ዙር ያደረገውን ድንቅ እንቅስቃሴ ማስቀጠል ከቻለ ዋንጫውን የማንሳት ዕድል ይኖረዋል፡፡ በጠባብ የጎል ልዩነት እያሸነፉ ሶስት ነጥብ ከጨዋታዎች የሰበሰቡት ድቻዎች ካደረጓቸው የመጨረሻ አምስት ጨዋታዎች አራቱን ሲያሸንፉ በአንዱ ብቻ ተሸንፈዋል፡፡ የመጀመሪያውን ዙር 6 ሳምንት ጨዋታዎች ያስተናገዱት ድሬዳዎች በበኩላቸው በደጋፊዎቻቸው ፊት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ አቅቷቸዋል፡፡ ካደረጉት ስድስት ጨዋታ አንዱን ብቻ ሲያሸንፉ ሁለት ጊዜ ተሸንፈው የተቀረውን አቻ ወጥተዋል፡፡

ግምት

ወላይታ ዲቻ በጠባብ የጎል ልዩነት ጨዋታውን ያሸንፋል፡፡

Saturday April 2

ቅዳሜ መጋቢት 24

ጅማ አባ ጅፋር ከሃዋሳ ከተማ

በሊጉ የመጨረሻ ጨዋታዎች ጥሩ የአቋም ለውጥ እያሳዩ የነበሩት ጅማዎች ከገቡበት የመውረድ አደጋ ለመውጣት አሁንም ራሳቸውን ማሻሻልና ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በሊጉ ያገኟቸውን ሶስት ብቻ ድሎች ማስመዝገብ የቻሉት በመጨረሻዎቹ ስድስት ጨዋታዎች ሲሆን ደረጃቸውንም ሰበታ ከተማን በመብለጥ ከ16ኛ ደረጃ ወደ 15ኛ ደረጃ አሳድገዋል፡፡ ሀዋሳ ከተማ በዋንጫ ፉክክር ቀጥተኛ ተሳትፎ ከሚያደርጉ ክለቦች አንዱ ነው፡፡ ቡድኑ በዘንድሮው ውድድር ከዋንጫ ባሻገር ለካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ለማለፍ ከወላይታ ድቻ ጋር ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

ግምት

ሀዋሳ ከተማ የተሻለ የማሸነፍ ግምት ቢሰጠውም ጅማ አባ ጅፋር ያልተጠበቀ ድል ሊያስመዘግብ ይችላል፡፡

BestBet Accumulator Bonus WIN UP TO 100%

X